በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ የመስራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ የመስራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ ተገለጸ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ለ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከመጡ አፍሪካውያን መሪዎች እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይህንን ፍላጎት ያንፀባረቀ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል። ሀገራቱ አየር መንገዶቻቸውን ለማሳደግና አየር መንገድ የሌላቸው ሀገራት ደግሞ ማቋቋም በሚችሉበት መንገድ ዙርያ ከአየር መንገዱ ጋር ውይይት እንዳደረጉ አክለው ገልፀዋል። በቅርቡ የናይጄሪያ የአቪዬሽንና የኤሮስፔስ ልማት ሚኒስትር ፌስቱስ ኬያሞ አየር መንገዱን መጎብኘታቸውንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያ የሚያደርጋቸውን በረራዎች እንዲያሳደግ መወያየታቸውንም አንስተዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0