አዲሱ የሳህል ሀገራት ሕብረት ኮንፌዴሬሽን ባንዲራ ለማሊ ፕሬዝዳንት ቀረበ

ሰብስክራይብ
አዲሱ የሳህል ሀገራት ሕብረት ኮንፌዴሬሽን ባንዲራ ለማሊ ፕሬዝዳንት ቀረበ የማሊ ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ ባንዲራውን የተቀበሉት የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን የሚኒስትሮች ልዑካንን በትላንትናው እለት በተቀበሉበት ወቅት ነው። የቡርኪናፋሶ መከላከያ ሚኒስትር ሴሌስቲን ሲምፖሬ "ይህን ውብ ባንዲራ ሁሉም የሳህል ሀገራት ሕብረት ህዝቦች እንዲያውቁት ይደረጋል" ብለዋል። ጉብኝቱ ባለፈው ሳምንት ባማኮ ውስጥ ተካሂዶ ከነበረው የሚኒስትሮች ልዑካን እና የባለሙያዎች ስብሰባ ተከትሎ የመጣ ነው። ስብሰባው በሳሕል ሀገራት ሕብረት እና ኤኮዋስ መካከል የሕብረቱ አባላት ከምእራብ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ የሚወጡበት መንገድ ላይ ያተኮረ ውይይት የተደረገበት ነው ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0