ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ለሚቀጥሉት አራት ወራት የኮባልት ማዕድን ወደ ውጭ እንዳይላክ አገደች

ሰብስክራይብ
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ለሚቀጥሉት አራት ወራት የኮባልት ማዕድን ወደ ውጭ እንዳይላክ አገደች ሀገሪቱ እርምጃውን የወሰደችው በዓለም ገበያ ያለውን ከፍተኛ የኮባልት ምርት አቅርቦት ለመቆጣጠር ነው። ከፍተኛ የሆነው የኮባልት አቅርቦት የምርቱ ዋጋ ያለማቋረጥ እንዲያሽቆልቆል ማድረጉ ተገልጿል። ውሳኔው "በማዕድኑ መነሻ እና የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ያለውን ቁጥጥር የማጠናከር እና ማዕድኑ በአካባቢው አቅም እንዲወጣ የማበረታታት" ዓላማ አለው ሲል የሀገሪቱ የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል። ይህ የእገዳ ውሳኔ በሶስት ወራት ውስጥ ሊገመገም እንደሚችል ኤጀንሲው ጠቁሟል። የመኪና ባትሪን ጨምሮ በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለውን የኮባልት ማዕድን ሶስት አራተኛ ለዓለም የምታቀርበው ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ናት። እገዳው ከጥር ወር ጀምሮ እንደ አዲስ ከተቀሰቀሰው የምስራቅ ኮንጎ ግጭት በኋላ የመጣ ነው። ከጥር ወር ጀምሮ አብዛኞቹ ሲቪሎች የሆኑ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁዲት ሱሚንዋ ቱሉካ በትላንትናው እለት በጄኔቫ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0