የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ እና ቻይና ግኑኝነት ጠንካራ መሠረት ጥሏል ተባለ ይህን የተናገሩት ዓለም አቀፍ ንግድን የማበረታታት ሃላፊነት የተጣለበትን የቻይና ምክር ቤት በምክትል ሊቀመንበርነት የሚመሩት ቼን ጂያንያን ናቸው። ባለሥልጣኑ ንግግሩን ያደረጉት ትናንት በተካሄደው የኢትዮ-ቻይና የንግድ ፎረም ላይ ነው። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ግኑኝነት በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደሆነች፤ በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ፣ እስያ እና ፓስፊክ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ንጉሥ ከበደ አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ በበኩላቸው፤ የቻይና እና የኢትዮጵያ ግንኙነት የሚገለጸው በኢኮኖሚ ትብብር ተጨባጭ ውጤቶችን በማስመዝገብ ነው ብለዋል። ምክትል ሊቀመንበር ቼን ጂያንያን፤ የቻይና እና የኢትዮጵያ ኩባንያዎች አዳዲስ የንግድ ትስስሮችን እንዲያስሱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጠንካራ መሰረት ጥሏል ሲሉም ተናግረዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ እና ቻይና ግኑኝነት ጠንካራ መሠረት ጥሏል ተባለ
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ እና ቻይና ግኑኝነት ጠንካራ መሠረት ጥሏል ተባለ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ እና ቻይና ግኑኝነት ጠንካራ መሠረት ጥሏል ተባለ ይህን የተናገሩት ዓለም አቀፍ ንግድን የማበረታታት ሃላፊነት የተጣለበትን የቻይና ምክር ቤት በምክትል ሊቀመንበርነት የሚመሩት ቼን ጂያንያን ናቸው። ባለሥልጣኑ... 25.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-25T12:59+0300
2025-02-25T12:59+0300
2025-02-25T15:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ እና ቻይና ግኑኝነት ጠንካራ መሠረት ጥሏል ተባለ
12:59 25.02.2025 (የተሻሻለ: 15:14 25.02.2025)
ሰብስክራይብ