የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና ጥምር ቡድኖች ተቀናቃኝ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችላቸውን ቻርተር ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና ጥምር ቡድኖች ተቀናቃኝ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችላቸውን ቻርተር ተፈራረሙ ቻርተሩን ከፈረሙት መካከል የሞሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወንድም ኮማንደር አብደልራሂም ዳጋሎ፣ የአማፂ ቡድን መሪ አብደላዚዝ አል-ሂሉ እና ከተለያዩ የፖለቲካ እና የጎሳ ቡድኖች የተውጣጡ ተወካዮች ይገኙበታል። የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በዝግ እንደተካሄደ ታውቋል። የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "የዘር አጥፊ ሚሊሻ እና የተከታዮቹን የመንግሥት ምስረታ ሴራ ያበረታታሉ" ሲል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶን ተችቷል። የትይዩ መንግሥት ምስረታው በቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል ተብሏል። አማፅያኑ “ከቀድሞው አገዛዝ ጋር የተሳሰሩ ሚሊሻዎች” ሲሉ የፈረጁትን የሱዳን ሰራዊት ጨምሮ፤ ነባሩን ኃይል በመበተን “አዲስ፣ የተዋሃደ እና ፕሮፌሽናል ብሔራዊ ጦር” ለማቋቋም እንዳቀዱ አስታውቀዋል። የሱዳን ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙርያ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም። የሱዳን መንግሥት ግን ኬንያ ሉዓላዊነቴን የሚያዳክም “አሳፋሪ አቋም” ይዛለች በማለት አምባሳደሩን ከናይሮቢ የጠራው በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0