በፈንታሌ ተራራ ታይቶ የማይታወቅ የሜቴን ጋዝ ልቀት ተገኘ የሳተላይት ምሥሎች በፈንታሌ ተራራ "ከፍተኛ መጠን ያለው ያልተለመደ" የሜቴን ጋዝ ልቀት እንዳገኙ ኒው ሳይንቲስት መጽሔት ዘግቧል። ግኝቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለውና ለወራት የዘለቀውን የእሳተ ጎመራ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመጣ ነው። የሚቴኑ መገኛ ምንጭ እስካሁን ግልጽ ባይሆንም፤ መጠኑ ከፍተኛ መሆኑ ሳይንቲስቶችን አስገርሟል። የሜቴን ልቀቱን ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 120 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በተከሰተው የእሳተ ጎመራ አቅራቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ የለየው የአውሮፓ ሕብረት ሳተላይት ነው። ግኝቱን ተከትሎ የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀቶች ክትትል አገልግሎት በሰራው ምርመራ፤ ከእሳተ ጎመራው የሚለቀቀውሜቴን በሰዓት 58 ቶን ያህል መጠን እንዳለውና ይህም በየቀኑ ከ20 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ገደማ የድንጋይ ከሰል ቃጠሎ ጋር እንደሚወዳደር አረጋግጧል። የመጊል ዩኒቨርሲቲ የእሳተ ገሞራ ተመራማሪ ጆን ስቲክስ እንዳስረዱት፤ እሳተ ገሞራዎች በተለምዶ እንደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና ሰልፈር ዳይኦክሳይድ ያሉ ጋዞችን የሚለቁ ቢሆንም፤ በዚህ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የሚቴን ልቀት ብዙ ጊዜ እንደማያጋጥም ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በፈንታሌ ተራራ ታይቶ የማይታወቅ የሜቴን ጋዝ ልቀት ተገኘ
በፈንታሌ ተራራ ታይቶ የማይታወቅ የሜቴን ጋዝ ልቀት ተገኘ
Sputnik አፍሪካ
በፈንታሌ ተራራ ታይቶ የማይታወቅ የሜቴን ጋዝ ልቀት ተገኘ የሳተላይት ምሥሎች በፈንታሌ ተራራ "ከፍተኛ መጠን ያለው ያልተለመደ" የሜቴን ጋዝ ልቀት እንዳገኙ ኒው ሳይንቲስት መጽሔት ዘግቧል። ግኝቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለውና ለወራት... 24.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-24T08:58+0300
2025-02-24T08:58+0300
2025-02-24T09:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий