የአፍሪካ ሀገራት የዓለም የቡና ምርት ድርሻቸውን በ2030 በ20% የማሳደግ ግብ አስቀመጡ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት የዓለም የቡና ምርት ድርሻቸውን በ2030 በ20% የማሳደግ ግብ አስቀመጡ ይህ ቁልፍ የውሳኔ ሃሳብ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች እና ባለድርሻ አካላት፤ የአፍሪካን የቡና ዘርፍ ማነቃቃት በሚቻልበት መንገድ ለመምከር በታንዛኒያ ዳሬሰላም ባካሄዱት ሶስተኛው የቡድን 25 የአፍሪካ ቡና ጉባዔ የቀረበ ነው። በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ከዓለም አቀፍ የቡና ምርት 11% ብቻ ትሸፍናለች - ይህም እ.አ.አ 1960ዎቹ ከነበረው በ25% ቀንሷል። የታንዛኒያ የግብርና ሚኒስትር ሁሴን ባሼ ለውጥ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ሶስት ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ቡና ወደ ውጭ ልከን፤ 50 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የቡና ምርት ማስገባት ማለት እብደት ነው። ከጥሬ ዕቃ ላኪነት እሴት ወደ መጨመር እና ወደ ያለቀ ዕቃ አምራችነት መቀየር አለብን" ሲሉ ተናግረዋል።ጉባዔው በአፍሪካ ውስጥ የቡና ንግድን በማሳደግ፣ ዝቅተኛ ምርታማነትን በመፍታት እና ወጣቱን ትውልድ ወደ ቡና እርሻ በመሳብ ላይ ያተኮረ ነበር። "የቡና ምርትን እምቅ አቅም ሳንጠቀም ስለ ሥራ አጥነት ማውራት አንችልም። ለወጣቶቻችን ሳቢ እንዲሆን ማድረግ አለብን" ሲሉ የኢንተር አፍሪካ ቡና ድርጅት ሊቀመንበር ፕሮስፔር ዶዲኮ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0