አፍሪካ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ ከሩሲያ ጋር ያልተገደበ የእህል እና የማዳበሪያ ንግድ እንዲኖራት ትፈልጋለች ተባለ

ሰብስክራይብ
አፍሪካ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ ከሩሲያ ጋር ያልተገደበ የእህል እና የማዳበሪያ ንግድ እንዲኖራት ትፈልጋለች ተባለ አፍሪካ ሩሲያን ጨምሮ ከእህል እና ከመዳበሪያ አቅራቢዎች ጋር ተደራድሮ የመግዛት ፍፁም ነፃነት እንዲኖራት ትፈልጋለች፤ ሲሉ የብራዛቪል ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ዣን-ኢቭ ኦሊቪዬር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት የቡድን 20 ሀገራት ሊቀመንበር ደቡብ አፍሪካ፤ ቀዳሚ የእህል እና ማዳበሪያ ላኪ ሀገር በሆነችው ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ተጥሎ ባለበት በዚህ ወቅት፤ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ እንደሆነ መግለጿን ተከትሎ ነው። "ችግሩ የአሜሪካ ማእቀብ ትኩረቱን በዋናነት በሩሲያ የእህል ምርቶች ላይ ማድረጉ ነው፤ ሆኖም ማዳበሪያንም ማንሳት አለብን። የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ማዳበሪያ ወሳኝ ነው። ሩሲያ የማዳበሪያ ምርትን በማቅረብ ረገድ ሚናዋ ከፍተኛ መሆኑን በደንብ የምናውቀው ጉዳይ ነው" ሲሉ የፋውንዴሽኑ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። በመሆኑም የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ ከሩሲያ ጋር ለመገበያየት ፍላጎት አላቸው ሲሉም አክለዋል። "ይህ የደቡብ አፍሪካ ብቻ አቋም ሳይሆን በአጠቃላይ የአፍሪካ የጋራ አቋም ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0