ኢትዮጵያ ከህንዱ የዲጂታል ላብራቶሪ ማሰልጠኛ ማዕከል ጋር የ10 ሚሊዮን ዶላር የትብብር ስምምነት ተፈራረመች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከህንዱ የዲጂታል ላብራቶሪ ማሰልጠኛ ማዕከል ጋር የ10 ሚሊዮን ዶላር የትብብር ስምምነት ተፈራረመች በህንድ ሀገር የሚገኘው ኢምፓወር የጤና ትምህርት ቤት የ10 ሚሊዮን ዶላር የዲጂታል ላብራቶሪ ማሰልጠኛ ማዕከል ለማቋቋም፤ ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። ስምምነቱ የኢትዮጵያን የመድኃኒት ዘርፍ የማጠናከር ዓላማ እንዳለው ተገልጿል። ማዕከሉ ለመድኃኒት አምራቾች ዘመናዊ የሥልጠና ማዕከል ሆኖ ከማገልገል ባለፈ፤ እንደ ወረርሽኝ ያሉ የሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ሲከሰቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ክትባት አምራችነት የመቀየር አቅም እንዳለው ተጠቁሟል። ከፕሮጀክቱ ትግበራ በፊት ተጨማሪ ውይይቶች እና የአዋጭነት ጥናቶች ይጠበቃሉ ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0