ኢትዮጵያ የቡድን 25 የአፍሪካ የቡና ጉባዔን እንድታስተናግድ ተመረጠች በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የቡድን 25 የአፍሪካ የቡና ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የአህጉሩን የቡና አቅም የሚያሳድጉ ምርምሮችና ትብብሮችን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎች እንደተላለፉ ገልጸዋል። ''የአፍሪካን የቡና ኢንዱስትሪ በማነቃቃት ለወጣቶች የሥራ ዕድሎችን መክፈት'' በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባዔ፤ ዘርፉን በሚያነቃቁ እና ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረናል ብለዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የቡና አምራች ሀገር እንደመሆኗ፤ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር ውጤት እያመጣች ትገኛለችም ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ጉባዔው ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ጥያቄ ተቀብሎ፤ የቡድን 25 የአፍሪካ የቡና ጉባዔ በ2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ወስኗል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ የቡድን 25 የአፍሪካ የቡና ጉባዔን እንድታስተናግድ ተመረጠች
ኢትዮጵያ የቡድን 25 የአፍሪካ የቡና ጉባዔን እንድታስተናግድ ተመረጠች
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ የቡድን 25 የአፍሪካ የቡና ጉባዔን እንድታስተናግድ ተመረጠች በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የቡድን 25 የአፍሪካ የቡና ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የአህጉሩን... 22.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-22T20:26+0300
2025-02-22T20:26+0300
2025-02-22T22:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий