የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የሩሲያ-አሜሪካ ውይይትን በተመለከተ ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሮናልድ ላሞላ ጋር ተወያዩ

ሰብስክራይብ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የሩሲያ-አሜሪካ ውይይትን በተመለከተ ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሮናልድ ላሞላ ጋር ተወያዩ "ሰርጌ ላቭሮቭ የኔቶ እና አውሮፓ ህብረት መሪዎች የዓመታት ዝግጅት ውጤት የሆነውን የዩክሬን ግጭት ለመፍታት የመንስኤውን ስር መሠረት ማስወገድ አስፈላጊ መሆኑን ጨምሮ፤ በሪያድ ሰለተደረገው የአሜሪካ-ሩሲያ ንግግር ውጤት ለደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሮናልድ ላሞላ ገለጻ አድርገዋል" ሲል የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሁለቱ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በጆሀንስበርግ ከተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ተገናኝተዋል። ሁለቱ ወገኖች ፍልስጤምን ጨምሮ በአንገብጋቢ ዓለም አቀፍ ጉዳዩች ዙርያ የመከሩ ሲሆን፤ በአፍሪካ በተለይም በታላቁ የሀይቅ አካባቢ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ተመሳሳይ አካሄድ እንደሚከተሉ እና ሰላምና ፀጥታን በተመለከተ አፍሪካ ሕብረት ለሚጫወተው ሚና እውቅና ሰጥተዋል። ሞስኮ እና ፕሪቶሪያ እንደ ተመድ፣ ብሪክስ፣ ቡድን 20 እና የሩሲያ-አፍሪካ ምክክር ባሉ ዓለም አቀፍ መድረኮች የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ትብብራቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባ መስማማታቸውንም ሚኒስቴሩ አክሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0