የቡድን 20 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዩክሬንን ጨምሮ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባ ስምምነት ላይ ደረሱ

ሰብስክራይብ
የቡድን 20 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዩክሬንን ጨምሮ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባ ስምምነት ላይ ደረሱ "በዓለም ዙሪያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ለኢኮኖሚ ልማት እና ለዘላቂ ልማት ግቦች (ኤስዲጂ) ስኬት ጎጂ እንደሆኑ አጽንኦት ተሰጥቷል። ጦርነቶች በትምህርት እና በጤና ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረ ተጠቁሟል፤ ግጭትን በዘላቂነት ለመከላከል እና ለሰላም ግንባታ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አስፈላጊ እንደሆነ ተሰምሮበታል። በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና አውሮፓ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶችን በተመለከት ሁሉም ሀገራት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርሆዎችን ተከትለው እንዲንቀሳቀሱ ስብሰባው አስረግጧል" ሲል መግለጫው ተነቧል። በተጨማሪም ተሳታፊዎቹ “የጂኦፖለቲካዊ ክፍፍል መስፋፋት” “የአለመተማመን መንፈስ” እንደፈጠረ እና ይህም ድህነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ወረርሽኞች፣ የኑክሌር መስፋፋት እና የትጥቅ ግጭቶችን በመዋጋት ረገድ የተገኙ መሻሻሎችን እንደሚሸረሽር መግባባት ላይ ደርሰዋል። ሚኒስትሮቹ የፋይናንስ እና የንግድ ስርዓቶችን ጨምሮ፤ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት እና ዓለም አቀፍ የአስተዳደር ስርዓቶችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግም አስረግጠዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0