ደቡብ አፍሪካ የአውሮፓ ፖለቲከኞችን ችላ በማለት ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ የአውሮፓ ፖለቲከኞችን ችላ በማለት ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ተናገሩ "በዓለም ላይ ካሉ ጋር ብዙ ሀገራት ጋር ግንኙነት አለን። ከነዚህም ሩሲያ አንዷ ናት። [...] ይሄኛውን ሀገር፤ ያኛውን ሀገር አግልል የሚል የውጭ ፖሊሲ የለንም። በብዙ ጉዳዮች ላይ ከሩሲያ ጋር መስራታችንን እንቀጥላለን" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ መሪ ሲሪል ራማፎሳ ከቡድን 20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል። የሩሲያ ሚዲያ ጋዜጠኛ እንደዘገበው፤ የአውሮፓ ህብረት የዲፕሎማሲ ሀላፊ ካጃ ካላስ ደቡብ አፍሪካ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር እንድታቆም ለማሳሳብ ሙከራ አድርገዋል። ካጃ ካላስ ከደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር ሐሙስ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ አውሮፓ ህብረት "በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዋጋ የሚሰጠው ተዓማኒ እና ተገማች አጋር ነው" ብለዋል። ካላስ በንግግራቸው በአውሮፓ ህብረት እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ከዚህ በፊት ተፈጥሮ ለነበረው ልዩነት፤ ፕሪቶሪያ በዩክሬን ግጭት ዙርያ ገለልተኛ አቋም መያዟ እና ከሩሲያ እና ቻይና ጋር የምታካሂደውን የጦር ልምምድ በምክንያትነት አንስተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0