ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሞስኮ ድጋፍ ሕገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖችን በመዋጋት ስኬታማ መሆን እንደቻለች ሩሲያ ገለጸች

ሰብስክራይብ
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሞስኮ ድጋፍ ሕገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖችን በመዋጋት ስኬታማ መሆን እንደቻለች ሩሲያ ገለጸች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሩሲያ ምክትል መልዕክተኛ አና ኢቭስቲኒግቫ፤ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ላይ ባተኮረው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር "ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ባንግዊ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በሁለትዮሽ አጋሮች በተለይም በሩሲያ በመታገዝ ሕገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖችን በመዋጋትና መንግሥት 90% የሚሆነውን የሀገሪቱን ግዛት በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች" ብለዋል። በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መረጋጋት ላይ መሻሻል እንዲሁም በሞስኮ እና በባንጊዊ መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ ቢቀጥልም፤ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት "የሩሲያ እርዳታን እያጥላሉ 'የሞተ ፈረስ መጋለባቸውን' ቀጥለዋል" ሲሉ የሩሲያው ልዑክ አክለዋል። "ሩሲያ ዘላቂ ሰላም እና ደህንነትን ለማስፈን፤ በጋራ መከባበር እና በእኩልነት ላይ ተመሥርታ ለወዳጇ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ትቀጥላለች" ሲሉ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0