ሩሲያ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት መደገፍ እንደምትችል ገለፀች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት መደገፍ እንደምትችል ገለፀች ሞስኮ ይህን ያለችው በሩሲያ ፌደሬሽን የኢኮኖሚ ልማትና ንግድ ሚኒስትር ማክሲም ሬሸትኒኮቭ የተመራ ልዑክ፤ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው። በውይይቱ በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ጠንካራ የንግድ ግንኙነት በሚፈጥሩ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳቦች ተነስተዋል። የሩሲያ ፌደሬሽን የኢኮኖሚ ልማትና ንግድ ሚኒስትር ማክሲም ሬሸትኒኮቭ፤ ሩሲያ ከሌላ ሀገራት የምትገዛውን የአበባ ምርት በቀጥታ ከኢትዮጵያ ለማስገባት እንደምትፈልግ እና ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ድርድርም ማገዝ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት እያደገ እንደሚገኝ እና በ2016 በጀት ዓመት ግብይቱ ከ389 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደደረሰ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0