ኢትዮጵያ 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔ ለማስተናገድ ዝግጁ እንደሆነች ገለጸች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔ ለማስተናገድ ዝግጁ እንደሆነች ገለጸች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን በተሳካ ሁኔታ እያስተናገደች የምትገኘው ኢትዮጵያ፤ በመጪው ሐምሌ ወር በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባዔ ታሰናዳለች። የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ፤ ቀጣዩን ጉባዔ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በመጠቀም ለጉባዔው የተሟላ ዝግጅት እንደምታደርግ ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልዑካን ቡድን መሪ እስጢፋኖስ ፎሽው፤ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያከናወነቻቸው ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን አድንቀዋል ሲል የገለፀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0