አሜሪካ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ጋር በተያየዘ በሩዋንዳ ሚኒስትር እና ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች

ሰብስክራይብ
አሜሪካ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ጋር በተያየዘ በሩዋንዳ ሚኒስትር እና ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች "ዩናይትድ ስቴትስ በምስራቅ ኮንጎ ከግጭት እና ከሰብዓዊ መብት ረገጣ ጋር በተገናኘ በሁለት ግለሰቦች እና ሁለት አካላት ላይ ማዕቀብ ጥላለች። ማዕቀቡ የሩዋንዳ የቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ጄምስ ካባሬቤ፣ የኤም23 እና የኮንጎ ወንዝ ጥምረት ቃለ አቀባይ ላውረንስ ካንዩካ እንዲሁም የካንዩካ ኩባንያዎች ኪንግስተን ፍሬሽ እና ኪንግስተን ሆልዲንግን ይመለከታል" ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃለ አቀባይ ታሚ ብሩስ አስታውቀዋል። ዋሽንግተን ሩዋንዳ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንድታከብር ጥሪ ያቀረበች ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት በሰብዓዊ መብት ረገጣ እና ጥቃት በመፈጸም የተሳተፉትን ተጠያቂ እንዲያደርጉ ታሳስባለች ሲሉም ባለስልጣኑ አክለዋል። "በሩዋንዳ ድጋፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ለስጋት፣ ጉዳት፣ ሞት እና መፈናቀል ተዳርገዋል፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ህይወታቸውን እንዲያጡ እና በርካቶች እንዲቆስሉ ሆነዋል" ያሉት ቃል አቀባዩ ብጥብጡ ወደ ሰፊ ክልላዊ ግጭት ሊያመራ ይችላል" ሲሉም ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0