በብሪታንያ ትችት የተሠነዘረባት ሩዋንዳ፤ በኮንጎ የሚደገፈው ሚሊሻ ለደህንነቴ ስጋት ነው ስትል ገለጸች ሩዋንዳ በኮንጎ ጦር ይደገፋል የምትለው የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ለደህንነቴ ስጋት ነው በማለት፤ በምስራቅ ኮንጎ እየወሰደች ያለውን እርምጃ ተከላክላለች። ይህም ብሪታንያ የሩዋንዳ ከፍተኛ ኮሚሽነርን ማክሰኞ እለት ጠርታ፤ ኪጋሊ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ድንበር ጥሳለች ስትል ክስ ማቅረቧን ተከትሎ የመጣ ነው። ሩዋንዳ የወሰደችውን እርምጃ እራስን መከላከል ነው ስትል ባወጣችው መግለጫ የገለፀች ሲሆን፤ ጥር 18 ቀን በምዕራብ ሩዋንዳ ሩባቩ ዲስትሪክት ለ16 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት አንስታለች። "ኤፍዲኤልአር በሩዋንዳ ግዛት ውስጥ ቢያንስ 20 ጥቃቶችን ፈጽሟል። በአሁኑ ሰዓት በኮንጎ ጦር ውስጥ እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር ተካቷል" ይላል በሩዋንዳ በኩል የወጣው መግለጫ። ኪጋሊ በተጨማሪም ቀውሱን የሚያባብሱ የጎሳ ግጭቶችን ችላ በማለት እና ስድስት የዘር ማጥፋት ተጠርጣሪዎችን በመሸሸግ ብሪታንያን ወንጅላለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤም23 አማፂያን በደቡብ አቅጣጫ በመገስገስ፤ ብሩንዲ ድንበር መቃረባቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ያመላክታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በብሪታንያ ትችት የተሠነዘረባት ሩዋንዳ፤ በኮንጎ የሚደገፈው ሚሊሻ ለደህንነቴ ስጋት ነው ስትል ገለጸች
በብሪታንያ ትችት የተሠነዘረባት ሩዋንዳ፤ በኮንጎ የሚደገፈው ሚሊሻ ለደህንነቴ ስጋት ነው ስትል ገለጸች
Sputnik አፍሪካ
በብሪታንያ ትችት የተሠነዘረባት ሩዋንዳ፤ በኮንጎ የሚደገፈው ሚሊሻ ለደህንነቴ ስጋት ነው ስትል ገለጸች ሩዋንዳ በኮንጎ ጦር ይደገፋል የምትለው የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ለደህንነቴ ስጋት ነው በማለት፤ በምስራቅ ኮንጎ እየወሰደች ያለውን... 21.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-21T14:12+0300
2025-02-21T14:12+0300
2025-02-21T14:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በብሪታንያ ትችት የተሠነዘረባት ሩዋንዳ፤ በኮንጎ የሚደገፈው ሚሊሻ ለደህንነቴ ስጋት ነው ስትል ገለጸች
14:12 21.02.2025 (የተሻሻለ: 14:44 21.02.2025)
ሰብስክራይብ