ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን የልማት ጥረት ድጋፍ እንዲያገኝ ከቡድን 20 ጋር በትብብር እንደምትሠራ ገለጸች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን የልማት ጥረት ድጋፍ እንዲያገኝ ከቡድን 20 ጋር በትብብር እንደምትሠራ ገለጸች ኢትዮጵያ፤ በወቅቱ የቡድን 20 ሊቀመንበር ደቡብ አፍሪካ ግብዣ፤ በጆሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች። በትናንትናው እለት በተጀመረው የቡድን 20 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፤ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር፣ ግጭት እና የአየር ንብረት ለውጥ የመሳሰሉ ፈተናዎችን ለመቅረፍ የቡድን 20 አባል ሀገራት ወሳኝ ሚና እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የታዳጊ ሀገራት በተለይም የአፍሪካውያን የመልማት ጥረት ድጋፍ እንዲያገኝ እና የዓለም አቀፍ ስርዓት ፍትሃዊ እንዲሆን፤ ከቡድን 20 አባል ሀገራትና ከዓመቱ ሊቀመንበር ደቡብ አፍሪካ ጋር በትብብር ትሰራለች ብለዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0