የናይጄሪያ ፓርላማ ዩኤስኤ አይዲ ለቦኮ ሃራም የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል መባሉን ሊመረምር ነው

ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ፓርላማ ዩኤስኤ አይዲ ለቦኮ ሃራም የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል መባሉን ሊመረምር ነው የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ስኮት ፔሪ፤ ዩኤስኤ አይዲ እንደ ቦኮ ሃራም ያሉ አሸባሪ ቡድኖችን በገንዘብ ይደግፋል ማለታቸውን ተከትሎ፤ የናይጄሪያ ሴኔት የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ኑሁ ሪባዱ እና የስለላ ኤጀንሲ ሃላፊዎች ማብራሪያ እንዲሰጡ መጥራቱን የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጎድስዊል አክፓቢዮ አስታውቀዋል። የሀገሪቱ ሕግ አውጭዎች የዩኤስኤ አይዲ ሚና ግልጽ መሆን እንዳለበት በማስረገጥ፤ ውንጀላውን በዝግ ስብሰባ እንደሚመለከቱ ነው የተገለጸው። የናይጄሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የገንዘብ ድጋፍ ምንጭ እና እንቅስቃሴ ለመመርመር ያቀደ ሲሆን፤ የፌደራል መንግሥት ከዩናይትድ ስቴትስ ማብራሪያ እንዲጠይቅም አሳስቧል። "ለሰው ህይወት መጥፋት፣ ለንብረት መውደም እና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት በሆነው የናይጄሪያ የጸጥታ ችግር ውስጥ የውጭ ተፅእኖ አለ የሚለው ክስ እውነት የሚሆን ከሆነ፤ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጸጥታ ስጋት እና ጥያቄዎችን ያስነሳል" ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ኢኑዋ ጋርባ ሐሙስ ዕለት ተናግረዋል። ሁለቱም ምክር ቤቶች ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ከደህንነት ኤጀንሲዎች ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0