ፑቲን በሩሲያ እና አሜሪካ መካከል ለተደረገው ወይይት መድረክ ላመቻቹት የሳዑዲ አረቢያ ልዑል አርጋ ወራሽ ምስጋና አቀረቡ

ሰብስክራይብ
ፑቲን በሩሲያ እና አሜሪካ መካከል ለተደረገው ወይይት መድረክ ላመቻቹት የሳዑዲ አረቢያ ልዑል አርጋ ወራሽ ምስጋና አቀረቡ ክሬምሊን በሩሲያ ፕሬዝዳንት እና መሐመድ ቢን ሳልማን መካከል ስለተደረገው የስልክ ውይይት በሰጠው መግለጫ፤ ሩሲያ እና ሳዑዲ አረቢያ በኦፔክ+ ማዕቀፍ ውስጥ በቅርበት ተባብረው መሥራታቸውን ይቀጥላሉም ብሏል። የሩሲያ-አሜሪካ የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ማክሰኞ እለት በሪያድ ተካሂዷል። እንደ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገለጻ፤ ከረጅም ጊዜ በኋላ በተደረገው የመጀመሪያው የፊት ለፊት ውይይት፤ ሁለቱ ወገኖች በሩሲያ እና አሜሪካ መካከል ግኑኝነት ዳግም እንዲጀመር እና የጋራ ተጠቃሚነት ባላቸው አዳዲስ ዘርፎች ለማስፋት ሁኔታዎችን ለመፍጠር ተስማምተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0