በኢትዮጵያ የሚገኘው የሩሲያ ማዕከል የሩሲያ ቋንቋን መማር ለሚፈልጉ አዳዲስ እድሎችን አቀረበ

ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የሚገኘው የሩሲያ ማዕከል የሩሲያ ቋንቋን መማር ለሚፈልጉ አዳዲስ እድሎችን አቀረበ ማዕከሉ በሩሲያ ቋንቋ እና ባህል ጥናት ዙርያ ሶስት ፕሮግራሞችን ይፋ አድርጓል። ከሶስት የሩሲያ ዩኒቨርስቲ የመጡ ተወካዮች በተቋማቸው ስለሚሰጡ የስልጠና ዓይነቶች ለተሳታፊዎች ገለጻ አቅርበዋል። የሩሲያ-አፍሪካ ኔትወርክ ዩኒቨርሲቲ ጥምረት የመረጃ ማዕከል፤ የአካዳሚክ ትብብርን በማጠናከር ለተማሪዎች እና ለተመራማሪዎች ግብዓቶችን እንደሚያቀርብ ገልጿል። የሴንት ፒተርስበርግ ኤሌክትሮቴክኒካል ዩኒቨርስቲ፤ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስለሚሰጠው የመዘጋጃ ኦንላይን ኮርሶች ገለጻ አቅርቧል። የኒዝኒ ኖቭጎሮድ የቋንቋ ጥናት ዩኒቨርስቲ የሩሲያ ቋንቋ ማዕከል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚሠራና ኢትዮጵያ ከሚገኘው የሩሲያ ማዕከል ጋር ሩሲያን ለማስተዋወቅ እንደሚተባበር ገልጿል። ሁሉም ተሳታፊዎች በዝግጅቱ ላይ ከተገኙ የዩኒቨርሲቲ እና ድርጅት ተወካዮች ጋር ግኑኝነት መፍጠር ችለዋል። የሩሲያ ባህላዊ የማርሻል አርት "ሳምቦ" የዝግጅቱ ድምቀት ነበር። አስደናቂ የነበረው የሳምቦ ትርዒት የስፖርቱን ዲሲፕሊን፣ ጥንካሬ እና ጥንታዊነት ያሳየ እንደነበር ነው የተገለጸው። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0