ስፑትኒክ የኢትዮጵያ ቢሮውን በይፋ በመክፈት በአማርኛ ቋንቋ መረጃዎችን የሚያቀርብ የመጀመርያው የሩሲያ ሚዲያ ሆነ በአዲስ አበባ በተካሄደው የስፑትኒክ ቢሮ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ፣ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኝሁ ተሻገር፣ የሩሲያ ቱዴይ የሚዲያ ቡድን ዋና ዳይሬክተር ዲሚትሪ ኪሴሌቭ እንዲሁም ሌሎች የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል። "የሩሲያ-ኢትዮጵያ እና የሩሲያ-አፍሪካ ግኑኝነቶችን ለማጠናከር ትልቅ እርምጃዎችን እየወሰድን ነው። የመረጃ ግኑኝነት፤ በእርግጥም ፍትሃዊ ለሆነና የአፍሪካን ሀገራት ጥቅም ሙሉ በሙሉ ከግምት ውስጥ የሚያስገባ፤ ባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ስርዓት ለመመሥረት ወሳኝ ነው ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የተከፈተው የስፑትኒክ ጽሕፈት ቤት ለሩሲያ የመገናኛ ብዙኃን የመጀመሪያ የሆነ ባለ ሁለገብ ተግባር የአርትዖት ማዕከል ነው። የሬዲዮ፣ የድረ-ገጽ፣ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ መተግበሪያዎች ይዘቶችን የማዘጋጀት እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ የዘጋቢ ስራዎችን ለመስራት እቅድ ተይዟል። በርካታ የአማርኛ ፕሮጀክቶች ከወዲሁ ተጀምረዋል። "ስፑትኒክ አላማውን እንደሚያሳካ እና የኢትዮጵያ መንግሥት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ እርግጠኛ ነኝ" ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል። ስፑትኒክ በአፍሪካ አህጉር ላይ በንቃት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በአህጉሪቱ ተፅዕኖውን እያስፋፋም ይገኛል። የሬዲዮ ፕሮግራሞቹን ናይጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ካሜሩን፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ጊኒ እና ዛምቢያ ውስጥ ባሉ የሬዲዮ ጣቢያዎች በእንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ያሰራጫል። ስፑትኒክ የአፍሪካ ሕብረት ብሮድካስቲንግ አባል እና የድርጅቱ የሬዲዮ ሽልማት አሸናፊም ነው። የስፑትኒክ ጋዜጠኞች ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመደበኛነት ቃለ መጠይቅ ያደርጋሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ስፑትኒክ የኢትዮጵያ ቢሮውን በይፋ በመክፈት በአማርኛ ቋንቋ መረጃዎችን የሚያቀርብ የመጀመርያው የሩሲያ ሚዲያ ሆነ
ስፑትኒክ የኢትዮጵያ ቢሮውን በይፋ በመክፈት በአማርኛ ቋንቋ መረጃዎችን የሚያቀርብ የመጀመርያው የሩሲያ ሚዲያ ሆነ
Sputnik አፍሪካ
ስፑትኒክ የኢትዮጵያ ቢሮውን በይፋ በመክፈት በአማርኛ ቋንቋ መረጃዎችን የሚያቀርብ የመጀመርያው የሩሲያ ሚዲያ ሆነ በአዲስ አበባ በተካሄደው የስፑትኒክ ቢሮ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ፣ የኢትዮጵያ... 19.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-19T20:50+0300
2025-02-19T20:50+0300
2025-02-19T21:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ስፑትኒክ የኢትዮጵያ ቢሮውን በይፋ በመክፈት በአማርኛ ቋንቋ መረጃዎችን የሚያቀርብ የመጀመርያው የሩሲያ ሚዲያ ሆነ
20:50 19.02.2025 (የተሻሻለ: 21:14 19.02.2025)
ሰብስክራይብ