ኢትዮጵያ እና ቬትናም የመጀመሪያውን የጋራ የፖለቲካ ምክክር በአዲስ አበባ አካሄዱ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቬትናም የመጀመሪያውን የጋራ የፖለቲካ ምክክር በአዲስ አበባ አካሄዱማክሰኞ እለት የተካሄደው የፖለቲካ ምክክር፤ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና በቬትናም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ኑየን ሚን ሄን መካከል የተደረገ ነው። አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ከቬትናም ፈጣን የኢንዱስትሪ እድገት ልምዶችን ለመቅሰም ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል የፈጠረ በመሆኑ የቬትናም ኩባንያዎች እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል። የቬትናም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን እንደገለጹ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0