የኢትዮጵያ ፓርላማ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሥራ ዘመን ለአንድ ዓመት አራዘመ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ፓርላማ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሥራ ዘመን ለአንድ ዓመት አራዘመ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የስራ ዘመኑን የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚያጠናቅቅ ቢሆንም፤ የጀመራቸውን ወሳኝ ሥራዎች እንዳላጠናቀቀ ፓርላማው ባካሄደው ስብሰባ ላይ ተገልጿል። በዚህም የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኮሚሽኑ የሥራ ዘመን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም የውሳኔ ሀሳቡን አቅርቧል። ምክር ቤቱም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ የኮሚሽኑ የሥራ ዘመን ለቀጣይ አንድ ዓመት እንዲራዘም ወስኗል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0