ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የኑክሌር ኢነርጂ ትብብራቸውን እንደሚቃኙ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች በርካታ የጋራ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። እነዚህም ከታች የተዘረዘሩትን ያካትታል፦ የአውቶሞቲቭ ምረት፣ የኬሚካልና ኤሌክትሪክ ምህንድስና፣ በምግብ ማቀነባበሪያ ትራንስፖርት መረጃ እና የቴሌኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች፣ ግብርና፣ ኢነርጂ። ማትቬዬንኮ በሰላማዊ የኑክሌር ኢነርጂ አተገባበር ዙርያ የትብብር አቅም እንዳለም ጠቁመዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየ ትብብር መኖሩን በመጥቀስ፤ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ አፍሪካ ውስጥ ለሩሲያ ወሳኝና ቁልፍ ከሆኑ አጋሮች ውስጥ አንዷ ናት" ያሉት አፈ ጉባዔዋ፤ ከ127 ዓመታት በፊት ከሩሲያ ጋር ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረተች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗ፤ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቦታ የሚያሳይ ነው ብለዋል። ማትቬዬንኮ በቅርቡ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ የሩሲያ-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ ሳይንሳዊ፣ ቴክኒካዊ ትብብር እና የንግድ ኮሚሽን ስብሰባ ለማካሄድ መታቀዱንም አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ ለሁለቱ ሀገራት የንግድ፣ የኢኮኖሚ እና የኢንቨስትመንት ግኑኝነት ኃይል እንደሚሆን ነው የተናገሩት።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የኑክሌር ኢነርጂ ትብብራቸውን እንደሚቃኙ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የኑክሌር ኢነርጂ ትብብራቸውን እንደሚቃኙ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የኑክሌር ኢነርጂ ትብብራቸውን እንደሚቃኙ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች... 19.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-19T10:56+0300
2025-02-19T10:56+0300
2025-02-19T11:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ የኑክሌር ኢነርጂ ትብብራቸውን እንደሚቃኙ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
10:56 19.02.2025 (የተሻሻለ: 11:14 19.02.2025)
ሰብስክራይብ