ኢትዮጵያ ለሩሲያ ቁልፍ አጋር ከሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ናት ሲሉ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለሩሲያ ቁልፍ አጋር ከሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ናት ሲሉ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ ዘንድሮ 127 ዓመታትን የሚያስቆጥረው የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመከባበር፣ በመተማመን እና በእኩል አጋርነት ላይ የተመሠረተ ታሪክ ያለው ነው ሲሉ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ ተናግረዋል።ማትቬዬንኮ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ብቸኛዋ የአፍሪካ ሀገር መሆኗ የተለየ ቦታ ያሰጣታል ያሉም ሲሆን፤ የሀገሪቱን ታሪካዊ የነፃነት ትግል እንዲሁም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጣሊያን ወረራ ወቅት የሩሲያ ኮሳኮች ለኢትዮጵያ ያደረጉትን ድጋፍ አንስተዋል። ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝን የመዋጋት ታሪክ አላቸው ያሉት አፈ ጉበኤዋ፤ አሁን ላይ ለፍትሃዊ የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም እንደሚታገሉ እና ለእኩልነት፣ መከባበር እና ብሔራዊ ሉዓላዊነት ቅድሚያ እንደሚሰጡ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ በሚነሱ ጉዳዮች የሩሲያን አቋም ከግምት ውስጥ ስለምታስገባ፤ በተለይም በዩክሬን ጉዳይ ለምትከተለው ሚዛናዊ አቋም ምሥጋናቸውንም ገልጸዋል። ማትቬዬንኮ ሞስኮ የኢትዮጵያን የብሪክስ ሙሉ አባልነት በመልካም ጎኑ እንደምትቀበል ገልፀው፤ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ፖለቲካዊ ትብብርን እንደሚያጠናክር፣ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያበረታታ እና የንግድ ልውውጥን እንደሚያመቻች ተናግረዋል። ሲያጠቃልሉም የሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት እያደገ መምጣቱን እና የሩሲያ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ጉብኝቱ ይህንን አዝማሚያ ለመደገፍ ቁርጠኝ እንደሆነ በመናገር፤ ስኬታማ ውጤት እንደሚገኝ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0