የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤር ባስ ጋር የበረራ ሰዓት አገልግሎት ውል ተፈራረመ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤር ባስ ጋር የበረራ ሰዓት አገልግሎት ውል ተፈራረመ ለሰባት ዓመታት የሚቆየው ስምምነት ኤርባስ ኤ350-900 እና ኤ350-1000 ሞዴሎችን ጨምሮ፤ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 24 ኤርባስ ኤ350 አውሮፕላኖች አጠቃላይ ጥገና መስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል። ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤርባስ የመሳሪያ ክምችቶችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችል እንዲሁም ለተለያዩ ወሳኝ ተቀያሪ የአውሮፕላን ክፍሎች የጥገና እና የምህንድስና ድጋፍ እንዲያገኝ ያስችለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርባስን ሰፊ የምህንድስና ዕውቀት በመጠቀም ዋስትናቸው የተረጋገጠ የአውሮፕላን ክፍሎችን እንደሚያገኝ፣ አስፈላጊ ክፍሎች በፍጥነት እንደሚደርሱት እና ከተመቻቸ የጥገና ሂደት ተጠቃሚ እንደሚሆን ተገልጿል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0