የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሩሲያ እና የአሜሪካ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን መካከል ከተደረገው ውይይት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሩሲያ እና የአሜሪካ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን መካከል ከተደረገው ውይይት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦ 🟠 ከአሜሪካ ተወካዮች ጋር በጣም ጠቃሚ ውይይት ተደርጓል። 🟠 አሜሪካ ለሞስኮ አቋም የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደጀመረች የሚያሳምን በቂ ምክንያት አለ። 🟠 ሩሲያ እና አሜሪካ በጂኦፖለቲካ ዘርፎች እና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ጥረቶችን ለማስተባበር ሁሉም ነገር መደረግ እንዳለበት ተስማምተዋል። 🟠 ሞስኮ እና ዋሽንግተን በኤምባሲዎቻቸው ስራ ላይ ያሉ ችግሮችን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለማስወገድ ተስማምተዋል። 🟠 ሩሲያ እና አሜሪካ በሞስኮ እና በዋሽንግተን አምባሳደሮችን ለመሾም ተስማምተዋል። 🟠 የዩክሬንን ግጭት የመፍታት ሂደት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንዲጀመር እና ተደራዳሪዎችን ለመሾም ከስምምነት ላይ ተደርሷል። 🟠 የሩሲያ እና አሜሪካ ተደራዳሪዎች ከተሾሙ በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል መደበኛ የሆነ ምክክር ይጀመራል።🟠 የሩሲያ ልዑካን ቡድን የኔቶ ወታደሮች በዩክሬን መገኘት ተቀባይነት እንደሌለው ለአሜሪካው ልዑክ አስረድተዋል። 🟠 የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ተስማምተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0