ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት ምስራቅ አፍሪካን ለማስተሳሰር እየሰራች ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት ምስራቅ አፍሪካን ለማስተሳሰር እየሰራች ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተዘጋጅቶ በነበረው ስምንተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ላይ ነው። በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፤ ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያካሄደችው አብዮት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በቅርቡ ያካሄደችው የኢኮኖሚ ሪፎርም የኢንቨስትመንት ፍላጎት እንዲጨምር በማድረግ፤ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ መነቃቃትን እንደፈጠረም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ምስራቅ አፍሪካን ለማስተሳሰር ጥረት እያደረገች ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የታላቁ ህዳሴና የኮይሻ የታዳሽ ኤሌክትሪክ ማምንጫ ግድቦች ለዚህ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0