ከበርካታ ኤጀንሲዎች የተውጣጣ የሩሲያ ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

ሰብስክራይብ
ከበርካታ ኤጀንሲዎች የተውጣጣ የሩሲያ ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነውበሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ቫለንቲና ማትቪዬንኮ የሚመራው የልዑካን ቡድን፤ የሩሲያ ፓርላማ የላይኛው ምክር ቤት ሴናተሮች እና የ14 ሚኒስቴሮች እና ኤጀንሲዎች ተወካዮችን ያካተተ እንደሆነ፤ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የፕሬስ አገልግሎት ገልጿል።የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበርዋ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከሁለቱም የኢትዮጵያ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔዎች ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ማትቪዬንኮ ከጉብኝቱ በፊት ከኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የጋራ ተጠቃሚነት እና ውጤታማ የሁለትዮሽ ትብብርን የሚያጠናክሩ የተለያዩ መስኮችን ማጎልበት ነው ብለዋል። በጉብኝቱ ውጤታማነት ላይ ያላቸውን እምነት የገለፁት ማትቪዬንኮ፤ ሩሲያ ለአስርት ዓመታት ለኢትዮጵያ ስትሰጥ የቆየችው ተከታታይ ድጋፍ ለቀጣዩ ግኑኝነት ስኬት ቁልፍ እንደሆነ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0