የግብፁ ፕሬዝዳንት ፍልስጤማውያንን ማፈናቀል ሳያስፈልግ ጋዛን መልሶ መግንባት የሚያስችል ሁሉንአቀፍ እቅድ እያዘጋጁ እንደሆነ ገለፁ

ሰብስክራይብ
የግብፁ ፕሬዝዳንት ፍልስጤማውያንን ማፈናቀል ሳያስፈልግ ጋዛን መልሶ መግንባት የሚያስችል ሁሉንአቀፍ እቅድ እያዘጋጁ እንደሆነ ገለፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታ አል- ሲሲ ይህን ያሉት ከዓለም የአይሁዳውያን ኮንግረንስ ሀላፊ ሮናልድ ሎደር ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። ውይይታቸው ቀጣናውን ማረጋጋት እንዲሁም የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት ትግበራ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር። አብደል ፋታ አል-ሲሲ የጋዛ ነዋሪዎች ሳይፈናቀሉ ጋዛን መልሶ መግንባት አስፈላጊ እንደሆነ አፅንኦት የሰጡ ሲሆን፤ ሁሉም አካላት የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዲያከብሩ አሳስበዋል። መካካር የሚፈጥረውን ስጋት የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ እ.አ.አ 1967 በነበረው ድንበር መሠረት እና ምስራቅ እየሩሳሌምን መቀመጫው ያደረገ የፍልስጤም መንግሥት ማቋቋም ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ብቸኛው መፍትሄ ነው ብለዋል። ሮናልድ ሎደር በበኩላቸው በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማምጣት ግብፅ ቁልፍ ሚና እንደምትጫወት እውቅና በመስጠት፤ በወሳኝ ጉዳዮች ዙርያ ከግብፅ ጋር ለመምከር ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0