ሩሲያ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዩክሬን በጋዜጠኞች ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት እንዲያወግዙ ጠየቀች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዩክሬን በጋዜጠኞች ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት እንዲያወግዙ ጠየቀች "የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት፤ በተለይም የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ፣ በአውሮፓ የደህንነት እና ትብብር ድርጅት የሚዲያ ነፃነት ተወካይ ጃን ብራቱ፣ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ እና ተመሳሳይ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፤ የኪዬቭ አገዛዝ ለፈፀመውተጨማሪ አረሜናዊ ወንጀል በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡ እና በጥብቅ እንዲያወግዙት እንሻለን" ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግርዋል። ሀላፊነት የሚሰማቸው መንግሥታት፤ የኪዬቭ አገዛዝ በሲቪሎች እና በመገናኛ ብዙሀን አባላት ላይ የሚፈፀመውን የሽብር ጥቃት እንዲያወግዙ ሞስኮ ጥሪ ታቀርባለች ሲሉም ዛካሮቫ አክለዋል። የሩሲያ ኩርስክ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳሪ አሌክሳንደር ኪንሽቲን በትላንትናው እለት እንደተናገሩት፤ የዩክሬን ጦር በቻናል ዋን የፊልም ቀረፃ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት አንድ የካሜራ ባለሙያ ጉዳት ደርሶበታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0