ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ቀውስ የሚውል 15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ቀውስ የሚውል 15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች ይህ የተገለፀው በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ተካሄዶ በነበረውና በሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ ባተኮረው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነው። ጉባዔውን ኢትዮጵያ፣ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት፣ አፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በጋራ እንዳዘጋጁት ተገልጿል። በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ኢትዮጵያ ለሱዳን ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የሚውል 15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሱዳን ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር፤ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0