ሩሲያ ለደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከ530 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ እገዛ ልታደርግ ነው "ሆስፒታሉን ዘመናዊ የሚያደርጉ እቅዶች ላይ እየሰራን ነው። በጥቂት ቀናት ውስጥ 50 ሚሊዮን ሩብል (530,000 ዶላር ገደማ) የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶች እናመጣለን። ቁሳቁሶቹም ሆስፒታሉን የሚያዘምኑ እና ያለበትን ተግዳሮቶች የሚፈቱ ናቸው" ሲሉ የሩሲያ የቀይ መስቀል ማህበር ሊቀመንበር ፓቬል ሳቭቹክ በማህበራዊ የትሥሥር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል። በተጨማሪም፤ ከሩሲያ መንግሥት በተሰጠው መመሪያ መሰረት ሆስፒታሉን የሚደግፍ እና የኢትዮጵያን ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰብዓዊ ድጋፍ ፈንድ ተመድቧል። የሩሲያ የቀይ መስቀል ማህበር ልዑክ የሰብዓዊነት እና የህክምና ፕሮግራሞች ላይ በጋራ መሥራት ላይ ያተኮረ ውይይት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አመራሮች ጋር ለማድረግም አቅዷል። የሩሲያ የቀይ መስቀል ማህበር ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል፤ በአፍሪካ የመጀመሪያው ባለብዙ ዘርፍ የሩሲያ የህክምና ማዕከል ነው። በሆስፒታሉ በዓመት ከ60 ሺህ በላይ ህመምተኞች ህክምና እንደሚያገኙ፤ የሩሲያ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ ለደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከ530 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ እገዛ ልታደርግ ነው
ሩሲያ ለደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከ530 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ እገዛ ልታደርግ ነው
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ ለደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከ530 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ እገዛ ልታደርግ ነው "ሆስፒታሉን ዘመናዊ የሚያደርጉ እቅዶች ላይ እየሰራን ነው። በጥቂት ቀናት ውስጥ 50 ሚሊዮን ሩብል (530,000 ዶላር ገደማ) የሚያወጡ የህክምና... 15.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-15T11:24+0300
2025-02-15T11:24+0300
2025-02-15T13:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ ለደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከ530 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ እገዛ ልታደርግ ነው
11:24 15.02.2025 (የተሻሻለ: 13:44 15.02.2025)
ሰብስክራይብ