ሱዳን በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ የነበራት ቦታ እንዲመለስ ጠየቀች

ሰብስክራይብ
ሱዳን በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ የነበራት ቦታ እንዲመለስ ጠየቀች "የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የሕብረቱን የሱዳን ግምገማ በድጋሚ እንዲያጤን እና ሱዳን በአህጉራዊው ድርጅት ውስጥ ወደ ነበራት ተፈጥሮአዊ ቦታ መመለሷ እና በአፍሪካ የነበራትን የመሪነት ሚና መልሳ ማግኘቷ አስፈላጊ እንደሆነ አሳስበዋል" ሲል የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዩሱፍ አል - ሻሪፍ፤ የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ባካሄደው አመፅ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ማድረጉን እና በሱዳን መንግሥት ላይ ጦርነት መክፈቱን ተከትሎ፤ ለአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደብዳቤ መላካቸውን ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ፤ መንግሥት ያቀረበው የድህረ ግጭት መልሶ ግንባታ ፍኖተ ካርታ፤ ከአፍሪካ ሕብረት ድጋፍ ጋር ተዳምሮ ሱዳን ወደ መረጋጋት እንድትመለስ ያስችላታል ብለዋል። "የአፍሪካ ሕብረት በሱዳን ውስጥ በሚታዩ ለውጦች አዎንታዊ ሚናውን መጫወት እንዲችል የሱዳን የሕብረቱ ሙሉ አባልነት መመለስ አለበት" ብለዋል።   የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ሱዳን በሲቪሎች ወደ ሚመራ የሽግግር መንግሥት እስክትመለስ ድረስ፤ እ.አ.አ ከጥቅምት 26፣ 2021 ጀምሮ ከአፍሪካ ሕብረት እንቅስቃሴዎች እንደታገደች ይታወሳል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0