ሞሮኮ ባጋጠማት የተራዘመ ድርቅ የከብት ሀብት ቁጥሯ የመመናመን ስጋት ተደቅኖባታል ተባለ

ሰብስክራይብ
ሞሮኮ ባጋጠማት የተራዘመ ድርቅ የከብት ሀብት ቁጥሯ የመመናመን ስጋት ተደቅኖባታል ተባለ የሞሮኮ በ2016 የነበራት የከብት እና የበግ ብዛት አሁን በ38% መቀነሱን የግብርና ሚኒስትሩን አህመድ ኤል ቦኦሪን ዋቢ አድርገው መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ለተከታታይ ስድስት አመታት ያጋጠመው ድርቅ የውሃ ማቆሪዎችን እንዳደረቀ፣ የግጦሽ ስፍራዎችን እንደቀነሰ እና በተጨማሪም ገበሬዎች ለቤት ውስጥ ፍላጎቶቻቸው ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ አስገድዷቸዋል ሲል ዘገባው ጨምሮ ገልጿል። በተያዘው የጎርጎሮሳውያኑ አዲስ ዓመት የተመዘገበው የዝናብ መጠን ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ከተመዘገበው አማካይ መጠን ጋር ሲነፃፀር በ53% ያነሰ በመሆኑ ምክንያት የተፈጠረው የግጦሽ መሬት እጥረት፤ ከብት፣ በግ እና ቀይ ስጋ ከውጪ እንዲገባ አድርጓል። ዋጋውን ለማረጋጋት የሞሮኮ መንግሥት የቁም ከብት እና ጥሬ ስጋ ላይ ይጣል የነበረውን የገቢ ቀረጥ እና ተጫማሪ እሴት ታክስ ለጊዜው ማንሳቱን ሪፖርቱ አመልክቷል። የተራዘመው ድርቅ ተፅእኖው ከእንሰሳት ሀብት ባለፈ፤ ዱካላ እና ሶኡስ - ማሳ የተባሉ ቁልፍ የግብርና ክልሎችን ያጠቃ ሲሆን፤ የመሰኖ ግድቦች ውሃ የመያዝ አቅም አሳሳቢ በሆነ ደረጃ በ2 እና በ15% ላይ ይገኛል። በአጠቃላይ የሀገሪቱ የግድብ ወሃ መጠን በ26% እንደቀነሰ እና ቅድሚያ እየተሰጠ የሚገኘው ለከተሞች የመጠጥ ውሀ ማቅረብ እንደሆነ ተገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0