አፍሪካ ላይ የተፈጠረውን ኢ-ፍትሃዊነት እና ታሪካዊ በደል ለማረም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊሻሻል ይገባል ሲሉ የዩኤን ኢሲኤ ሃላፊ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
አፍሪካ ላይ የተፈጠረውን ኢ-ፍትሃዊነት እና ታሪካዊ በደል ለማረም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊሻሻል ይገባል ሲሉ የዩኤን ኢሲኤ ሃላፊ ተናገሩ በ #38ኛውየአፍሪካሕብረትጉባዔ የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ሃላፊ ክላቨር ጋቴ "የወቅቱ ዓለም አቀፋዊ የፋይናንስ መዋቅር ጊዜ ያለፈበት፣ ኢ-ፍትሐዊ እና አድሏዊ በመሆኑ ግቡን እንዲመታ መሻሻል አለበት። [...] አፍሪካ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ ረገድ ጠንካራ ድምጽ እንዲኖራት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የአስተዳደር ማሻሻያዎችን ማድረግ ያስፈልጋል" ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት ከፍ ያለ ወለድ ከመክፈል ይልቅ ለልማትና ኢንቨስትመንትን ቅድሚያ እንዲሰጡ የዕዳ ሽግሽግ ማድረግ ቁልፍ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል። የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ አቅም የሚገመግም አፍሪካ መር የብድር ደረጃ አውጪ ኤጀንሲ ማቋቋም አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል። "የአፍሪካን ህዝብ፣ ሀብትና ክብር የሰረቀውን እና በዓለም አቀፍ የገንዘብ ሥርዓት፣ የንግድ መዋቅሮች እና የአስተዳደር ተቋማት ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ የቀጠለ ልዩነቶችን ትቶ ያለፈውን የአትላንቲክ ባሪያ ንግድ እና የቅኝ አገዛዝ ብዝበዛን እውነታ መካድ አንችልም" ሲሉ ያብራሩት ጋቴ፤ ይህ ታሪካዊ የፍትህ ጉድለት አፍሪካ እንዳትለማ፣ ኢኮኖሚያዋ እንዳያድግ እና ንግድ እና ኢንቨስትመንት ላይ ሥርዓታዊ እንቅፋቶች እንዲፈጠር አድርጓልም ብለዋል። ለነዚህ የቆዩ ልዩነቶች መፍትሄ የሆነው የማካካሻ ፍትህ ከገንዘብ ካሳ የተሻለ መሆን እንዳለበትም ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0