የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ ከቡድን 8 የሀገራት ስብስብ እንድትወጣ መደረጉ ስህተት ነው አሉ

ሰብስክራይብ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ ከቡድን 8 የሀገራት ስብስብ እንድትወጣ መደረጉ ስህተት ነው አሉ "ሩሲያ እንድትመለስ እፈልጋለው፤ እንድትወጣ መደረጉ ስህተት ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ለጋዜጠኞች የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ፤ ሩሲያ በቡድን-8 ውስጥ ብትሆን ኖሮ "ከዩክሬን ጋር የተፈጠረው ችግር አይኖርም” ነበር ብለዋል። ቡድን-7 ወሬው ሁሉ ስለ ሩሲያ ነው ያሉት ትራምፕ፤ ሞስኮ በቡድኑ ጠረጴዛ ዙርያ ቦታ ሊኖራት ይገባልም ብለዋል። "ምን እያደረጋችሁ ነው? ብያቸዋለሁ...ስለ ሩሲያ ብቻ ነው የምታወሩት፣ ስለዚህ በጠረጴዛው ላይ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል። ፑቲን መመለስ የሚፈልግ ይመስለኛል” ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0