ከአሜሪካ፣ ሩሲያ እና ዩክሬን የተወጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመጪው ሳምንት በሳዑዲ አረቢያ እንደሚመክሩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ከአሜሪካ፣ ሩሲያ እና ዩክሬን የተወጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመጪው ሳምንት በሳዑዲ አረቢያ እንደሚመክሩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ "ይህንን ጦርነት ማስቆም የምንችልበትን መንገድ እናያለን" ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አክለው ተናግረዋል። በተጨማሪም ከሩሲያ፣ ዩክሬን እና አሜሪካ የተውጣጡ የከፍተኛ ደረጃ ተወካዮች፤ በዛሬው እለት ከሚካሄደው የሙኒክ የደህንነት ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ለውይይት እንደሚቀመጡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጨምረው ተናግረዋል። ሆኖም ዩክሬን በኮንፈረንሱ ላይ ከሩሲያ ተወካዮች ጋር እንደማትደራደር፤ የዘለንስኪ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ዲሚትሮ ሊትቪን ተናግረዋል። "ዩክሬን በመጀመሪያ ከአሜሪካ ጋር መነጋገር አለባት። ለእውነተኛ እና ዘላቂ ሰላም፤ አውሮፓ በየትኛውም ንግግር ላይ መሳተፍ አለባት። ሁሉም የተስማማበት የጋራ አቋም ነው ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ሊቀርብ የሚገባው"  ሲሉ አማካሪው አስረግጠዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0