ኢትዮጵያ በስነ-ተዋልዶ ላይ ባካሄደችው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የእናቶችን እና የህፃናትን ህልፈት መቀነስ ችላለች ሲሉ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ገለፁ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በስነ-ተዋልዶ ላይ ባካሄደችው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የእናቶችን እና የህፃናትን ህልፈት መቀነስ ችላለች ሲሉ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ገለፁ የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር መቅደስ ዳባ ይህን ያሉት በትላንትናው እለት በተካሄደው የኔፓድ የሚኒስትሮች መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ፤ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች ልምድ የሚለዋወጡበት እና በትብብር መስራት የሚያስችላቸው መግባባት የሚፈጥሩበት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በስነ-ተዋልዶ ዘርፍ ላይ ባካሄደችው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት፤  የእናቶችን እና የህፃናትን ህልፈት መቀነስ እንደተቻለ እና የጤና ስርዓቱም እንደተሻሻለ ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት ተናግረዋል። አክለውም አፍሪካ በጤናው ዘርፍ ላይ የሀገር ውስጥ ምርቷን በማሳደግ ራሷን ለመቻል መስራት ይገባታል ብለዋል። በመድረኩ 24 ቅድሚያ የሚሰጣቸው መድሀኒቶችን በአህጉሪቷ ለማምረት የሚያስችል ስምምነት በአውዳ ኔፓድ እና ቻይ በተሰኘው ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መካከል ተፈርሟል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0