ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችው የንግድ እና የወደብ ስምምነት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ገለፀች

ሰብስክራይብ
ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችው የንግድ እና የወደብ ስምምነት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ገለፀችዱባይ በተካሄደው የ2025 የዓለም መንግሥታት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ኢሮ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰው የባህር እና የንግድ ስምምነት በዚህ ዓመት መጨረሻ እንደሚጠናቅቅ መግለፃቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የበርበራ ወደብን ስትራተጂካዊ ጠቀሜታ በንግግራቸው ያነሡት ኢሮ፤ ዲፒ ወርልድ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኩባንያ 400 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት በመመደብ ባካሄደው ልማት ወደቡ እንደተሻሻለ ጠቁመዋል። የታደሰው የበርበራ ወደብ በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጋሎት ላይ ይውላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0