የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለገንዘብ ስርዓት ማሻሻያ እና ለአፍሪካ አንድነት ጥሪ አቀረቡ "እኛ [አፍሪካውያን] የአፍሪካን እድገት የሚደግፍ እና አህጉሪቱ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች ስኬታማ በሆነ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት እንዲፈጠር እንጠይቃለን። የአየር ንብረት ፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ማግኘት እንድንችል እንጠይቃለን" ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። አብዛኛዎቹ ተግዳሮቶች የጋራ መፍትሄዎችን ይፈልጋሉ ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለአፍሪካ እና ለደቡባዊ ዓለም ሀገራት የባለብዙ ወገን ግኑኝነት ምርጫ ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል። የአህጉሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ለመቅረፍ በጋራ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አንድነት እና አብሮነት ወሳኝ ነው ብለዋል። ሚኒስትሩ አክለውም የአፍሪካ ሕብረትን የመሰሉ አህጉራዊ ድርጅቶችን በመጠቀም፤ የአፍሪካ ሕብረትን አህጉራዊ የልማት እቅድ እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን ጨምሮ የጋራ ውጥኖችን ማሳካት አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሃፊ ክላቨር ጌቴ በበኩላቸው፤ አሁን በሥራ ላይ ያለው የዓለም የፋይናንስ መዋቅር ጊዜ ያለፈበት፣ ኢፍትሃዊ እና የተዛባ ነው ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት የተጋነነ ወለድ ከመክፈል ይልቅ በልማት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችል የዕዳ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለገንዘብ ስርዓት ማሻሻያ እና ለአፍሪካ አንድነት ጥሪ አቀረቡ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለገንዘብ ስርዓት ማሻሻያ እና ለአፍሪካ አንድነት ጥሪ አቀረቡ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለገንዘብ ስርዓት ማሻሻያ እና ለአፍሪካ አንድነት ጥሪ አቀረቡ "እኛ [አፍሪካውያን] የአፍሪካን እድገት የሚደግፍ እና አህጉሪቱ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች ስኬታማ በሆነ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዓለም አቀፍ የፋይናንስ... 13.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-13T16:55+0300
2025-02-13T16:55+0300
2025-02-13T17:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለገንዘብ ስርዓት ማሻሻያ እና ለአፍሪካ አንድነት ጥሪ አቀረቡ
16:55 13.02.2025 (የተሻሻለ: 17:14 13.02.2025)
ሰብስክራይብ