ትራምፕ የዩክሬን የኔቶ አባልነት ጥያቄ ከድርድር ውጪ መሆኑን እንደሚቀበሉ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ትራምፕ የዩክሬን የኔቶ አባልነት ጥያቄ ከድርድር ውጪ መሆኑን እንደሚቀበሉ ተናገሩ ትራምፕ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴዝ የዩክሬንን የኔቶ አባልነት አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ሲጠየቁ "በእኔ በኩል እቀበለዋለሁ፤ ተግባራዊ ነው ብዬ አላምንም" ብለዋል። ትራምፕ አክለውም ሩሲያ፤ ዩክሬን የኔቶ አባል እንድትሆን እንደማትፈቅድ ለረዥም ጊዜ ይዛ የቆየችው አቋም እንደሆነ ተናግረዋል። እሮብ እለት ባደረጉት ንግግር የዩክሬን ጦርነት "መቆም አለበት" ያሉት የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሄግሴዝ፤ ዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ኔቶን መቀላቀል ግጭቱን ይፈታል ብላ እንደማታምን አስታውቀዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን እንደማትልክ አረጋግጠው፤ እንዲህ ዓይነት ስምሪት በኔቶ የመመስረቻ ስምምነት የጋራ መከላከያ አንቀፅ (አንቀፅ 5) ስር እንደማያርፍ አስረድተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0