ኢትዮጵያ ከቱኒዚያ እና ሞሮኮ ጋር የሁለትዮሽ ግኑኝነቷን ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙርያ መከረች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከቱኒዚያ እና ሞሮኮ ጋር የሁለትዮሽ ግኑኝነቷን ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙርያ መከረች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፤ ከ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ከቱኒዚያ እና ሞሮኮ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል። ከቱኒዚያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ አሊ ናፍቲ ጋር ባደረጉት ውይይት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ ኢነርጂ፣ አይሲቲ እና ትምህርት መስኮች በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል። ከሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ስለማጠናከር ሀሳብ እንደተለዋወጡ እና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ለማካሄድ እንደስማሙ፤ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0