ፑቲን እና ትራምፕ በስልክ ውይይታቸው ያተኮሩባቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦

ሰብስክራይብ
ፑቲን እና ትራምፕ በስልክ ውይይታቸው ያተኮሩባቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦ ▪ ፑቲን የዩክሬን ግጭት መንስኤዎችን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ለትራምፕ ነግረዋቸዋል። ▪የሩሲያው ፕሬዝዳንት ለዩክሬን ጉዳይ ዘላቂ እልባት ለማግኘት ድርድር መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ከትራምፕ ጋር ተስማምተዋል። ▪ፑቲን እና ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ እና በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙርያም ተወያይተዋል። ▪የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከፑቲን ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ የጉብኝት ልውውጥ ለማድረግ መስማማታቸውን ገልጸዋል። ▪ፑቲን እና ትራምፕ በሩሲያ እና በአሜሪካ ዜጎች ልውውጥ ዙርያ ተወያይተዋል፤ ዋሽንግተን የተደረሱትን ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ዋስትና ሰጥታለች። ▪የሩሲያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ሩሲያ ውስጥ ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ለትራምፕ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0