ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳበች ይህ የኢንቨስትመንት እድገት የንግድ ምህዳሩን ለማቀላጠፍ እና ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ ዘርፎችን ለመክፈት፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት የተተገበሩ ከ80 በላይ ማሻሻያዎች ውጤት ነው ተብሏል። ሀገሪቱ የንግድ ሕግ በማሻሻል፣ የካፒታል ገበያ ሕግን በማስተዋወቅ፣ የኢ-ግብይት ሕግን በማፅደቅ ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ በተለይም ከ50 ዓመታት በላይ ዝግ ሆኖ የቆየው የሀገሪቱ ንግድ ዘርፍ መከፈቱን እና የውጭ ባለሀብቶች አሁን በጅምላ፣ በችርቻሮ፣ በገቢ እና በወጪ ንግድ እንዲሳተፉ መደረጉን አንስተዋል። አንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6.4% ብልጫ አለው። ይህ እድገት ከኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ፣ ሰፊ ገበያ (ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ)፣ ርካሽ የሃይል ሃብት አቅርቦት እና በደንብ ከበለፀጉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጋር ተዳምሮ፤ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ገበያ ላይ እምነታቸው እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል ሲሉ ኮሚሽነሩ አክለዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት 1.
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት 1.
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳበች ይህ የኢንቨስትመንት እድገት የንግድ ምህዳሩን ለማቀላጠፍ እና ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ የነበሩ ዘርፎችን ለመክፈት፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት... 12.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-12T18:38+0300
2025-02-12T18:38+0300
2025-02-12T19:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий