ኢትዮጵያ እና ህንድ የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ህንድ የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ ሁለቱ የብሪክስ አባል ሀገራት በአቅም ግንባታ፣ በመከላከያ ጥናትና ምርምር፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች፣ በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙርያ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ እና የህንድ አቻቸው ራጃንታ ሲንግ እንደፈረሙት የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ነው የዘገበው። የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ህንድ ባዘጋጀችው ኤሮ 2025 ኤግዚቢሽን በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0