በዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቁጥጥር ስር የነበረ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ህይወቱ አለፈ

ሰብስክራይብ
በዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቁጥጥር ስር የነበረ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ህይወቱ አለፈ የ45 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ገዛኸኝ ደጀኔ በአሪዞና ግዛት ፊኒክስ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ እንዳለፈ ባለሥልጣኑ አስታውቋል። ገዛኸኝ ወደ አሜሪካ የገባው ነሐሴ 13፣ 2016 የነበረ ሲሆን በድንበር ጠበቂዎች ተይዞ የጥገኝነት ጥያቄውን በኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት እየተከታተለ እንደነበር ታውቋል። ኢትዮጵያዊው ስደተኛ የደም ካንሰር ምርመራ ተደርጎለት ውጤቱን እየተጠባበቀ እንደነበርም የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0