በሃላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሰብስክራይብ
በሃላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ዋለበአፋር እና ኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎች በሚገኘው ሃላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ ላለፉት ሶስት ቀናት የእሳት ቃጠሎ ተከስቷል።የእሳት ቃጠሎውን ለመቆጣጠር በሎደር የታገዘ እሳት የማጥፋት እና የቆረጣ ስራ ተሰርቷል። ደረቅ የአየር ንብረት እና በአካባቢው ያለው ከፍተኛ ንፋስና ደረቅ ሣር ለእሳቱ መባባስ ምክንያት እንደነበር ተገልጿል። የእሳት ቃጠሎው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ርብርብ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ መቆጣጠር እንደተቻለ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0